እንኳን ወደ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፍትህ ፅ/ቤት በደህና መጡ
ራዕይ
በ2022 በኢትዮጵያ የፍትሕ ተቋማት ተምሣሌት ሆኖ ማየት
ተልዕኮ
የከተማ አስተዳደሩንና የነዋሪውን መብትና ጥቅም በማክበርና በማስከበር፣ ንቃተ ሕግ እንዲዳብር በማድረግ፣የሕግ ተፈፃሚነትን በማረጋገጥ የላቀ የፍትህ አገልግሎት መስጠት፡፡
ተግባርና ኃላፊነት
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ፍትህ ፅ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 84/2016 አንቀጽ 11 ንዑስ-አንቀጽ 9 መሠረት የተቋቋመ ሲሆን በዚሁ አዋጅ አንቀፅ 25 ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት ውስጥ የክ/ከተማው አስተዳደር ዋና የህግ አማካሪና ሕጋዊ ወኪል በመሆን በየትኛውም የዳኝነት እርከን በመቅረብ የፍትሕብሔር ክርክር በማድረግ የከተማ ነዋሪዉንና የአስተዳደሩን መብት እና ጥቅም ማስጠበቅ፤ የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የከተማዉን የፍትሕ ማሻሻያ ፕሮግራም ይተገብራል፡፡ ይህን ሲተገብር የሲቪል ማህበረሰብና የነዋሪዉን ተሳትፎ ለማጎልበት የተለያዩ አደረጃጀትና አሰራሮችን ይተገብራል፡፡ በአዋጁ ከተሰጡት ዋና ዋና ስልጣንና ተግባራት የህግ ተፈፃሚነትን ማረጋገጥ ፤ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን ህጋዊነት ማረጋገጥ ፤ የነዋሪዉን ንቃተ-ህግ ማሳደግ፣ የተለያዩ አስተዳደሩ የሚያደርጋቸዉን አስተዳደራዊ ዉሎች የማዘጋጀት፣ ረቂቅ ውል ማዘጋጀት፣ ሰብዓዊ መብትን ከማክበርና ከማስከበር አንፃር የክ/ከተማዉን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ዕቅድ በማዘጋጀት መተግበርና በማስተገበር በክ/ከተማዋ የህገ-ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በፌደራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣዉን አዋጅ ለማስፈፀም የማስተባበር ሥልጣንና ተግባራትን ያካተተ ነው፡፡