Welcome to Akaki Kality Sub City Justice Office
እንኳን ወደ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፍትህ ፅ/ቤት በደህና መጡ
Home
News
About Laws
Log In
Admin
Data Encoder
Prosecutor
Dir/Head
Chief
የሥራ ቦታ ዝውውርን ሠራተኛን ለማሰናበት በእጅአዙር መጠቀም
በአሠሪ እና ሠራተኛ ሕጉ መሠረት አሠሪው ሠራተኛውን ከቦታ ቦታ አዘዋውሮ የማሠራት ሥልጣኑ እስከ ምን ድረስ ነው? አሠሪ በቂ ምክንያት ሳይኖረው ሠራተኛውን ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ ማዘዋወር ይችላል? ሠራተኛው በአዲሱ የሥራ ቦታ ለመገኘት የማይችልበት በቂ ምክንያት ቢኖረው እና በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ሪፖርት ሳያደርግ ቢቀር የሚኖረው ሕጋዊ ውጤት ምንድን ነው? በጉዳዩ የሰበር ችሎት አቋምስ ምን ይመስላል? በኢትዮጵያ አሠሪና ሠራተኛ ሕግ እንዲሁም በሰበር ችሎት የተሰጡ አስገዳጅ ውሳኔዎች ለቀጣሪዎች የተለጠጠ ሠራተኛን የማስተዳደር ሥልጣን (Managerial prerogative) ይሰጣሉ፡፡ በመሆኑም አንዳንድ አሠሪዎች የሥራ ቦታ ዝውውርን እንደሁነኛ ሠራተኛን የመቅጫ መንገድ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡ አሠሪ ሠራተኛውን ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ሲያዘዋውር ሠራተኛው ቅሬታ ቢኖረው እንኳን ወደተዘዋወረበት ቦታ ሔዶ ሥራ ከጀመረ በኋላ ክስ ማቅረብ ከመቻሉ በቀር ባለበት ቦታ ቅሬታውንም ይሁን ክሱን ማቅረብ አይችልም፡፡ የሰበር ችሎት በመዝገብ ቁጥር 37778፣ 38189 እና በሌሎች መዝገቦች በሰጠው ውሳኔ አንድ ሠራተኛ የዝውውርን ትእዛዝ ባለመቀበል ለአምስት ተከታታይ ቀናት አዲስ ወደተመደበበት የሥራ ቦታ ላይ ሪፖርት ካላደረገ እና ሥራውን ካልጀመረ በአሠሪና ሠራተኛ ሕጉ አንቀጽ 27 መሠረት ለሥራ ስንብት ምክንያት እንደሚሆን ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ የሰበር ችሎት በመ/ቁ 37778 (ቅጽ 8 ኅዳር 4 ቀን 2001) በአሠሪ በተደረገ የሥራ ዝውውር ቅሬታ አድሮብኛል በሚል ምክንያት ከሥራ መቅረት የሕግ ድጋፍ እንደሌለው ሲገልጽ በሰ/መ/ቁ 41623 (ቅጽ 8 መጋቢት 8 ቀን 2001) ላይ ደግሞ በአሠሪው ወደሌላ ቦታ ተዘዋውሮ እንዲሠራ የተደረገ ሠራተኛ ዝውውሩን በወቅቱ ሳይቃወም የተዘዋወረበት የሥራ ገበታ ላይ ሠራተኛው በተዘዋወረበት ቅርንጫፍ ለመገኘት የሚፈጅበትን ጊዜ ግምት ውስጥ በማስገባት ( ሰበር ችሎት በመ/ቁ 125004 ቅጽ 20 )ለ 5 ተከታታይ ቀናት የቀረ እንደሆነ የሥራ ውሉን ለማቋረጥ በቂ ምክንያት እንደሆነ ያትታል፡፡ በዝውውር ምክንያት የሥራ ውል የመቋረጥ አግባብነት ጭብጥ ሆኖ በተያዘበት የሰ/መ/ቁ 238
Read More