Welcome to Akaki Kality Sub City Justice Office

እንኳን ወደ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፍትህ ፅ/ቤት በደህና መጡ

በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት አፈፃፀም

በፍትህ ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት በፍትሃብሄር 492 መዛግብት ክርክር የተደረገባቸው ሲሆን ከዚህ ውስጥ 124 መዛግብት ውሳኔ ተሰጠበትን 112 መዛግብት ለመንግስት የተወሰኑ ሲሆን 11 መዛግብት በይግባኝ ተጠይቆባቸው በሂደት ላይ ናቸው፡፡ 1 መዝገብ የማያዋጣና በቀጣይ መሄድ ሳያስፈልገው በፓናል ተዘግቷል ፡፡ ለመንግስት ከተወሰኑ መዛግብት ላይ በገንዘብ ለመንግስት የተከበረ ጥቅም 134,659,000 (አንድ መቶ ሰላሳ አራት ሚሊዮንስድስ መቶ ሃምሳ ዘጠን ሺህ ብር) በዓይነት የተከበረ ጥቅም 84 ሺህ ካሬ ሜትር ይዞታና 8 የመንግስት ቤት ተከብሯል፡፡ 52 ነጻ የፍትሃብሄር የህግ ድጋፍ ለሚፈልጉ ግለሰቦች ድጋፍ የተሰጠ ሲሆን የደንብ ጥሰት 165 መዛግብት የቀረበ ሲሆን 165 አፈፃፀም ተከፈተና 74 ተፈጽሟል ከዚህ ለመንግስት የተገኘ ገቢ 227,900 ሁለት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ ዘጠን መቶ ብር ለመንግስት ገቢ እንዲደረግ ተደርጓል፡፡ ከወንጀል ህግ አፈጻጸም አንጻር 696 የበግል አቤቱታ አቅራቢ379 የደንብ መተላለፍ 317 መዛግብት የተመረመረና ውሳኔ የተሰጠባቸው ሲሆን ከቀረበው የግል አቤቱታ መዛግብት ውጥስጥ 300 በጣቢያ 23 በፍርድ ቤት 17 በጽ/ቤት በዕርቅ በመዘወጋት 87.5 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡ ሌሎች የደንብ መተላለፍ ወንጀሎች 417 መዛግብት በፍርድ ቤት ውሳኔ ያገኘ ሲሆን ከዚሁ የቅጣት ለመንግስት ገቢ 133,500 አንድ መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር ገቢ ተገንቷል፡፡ ከንቃተ ህግ ማሰደግ አንጻር በ11 የህግ ርዕሶች ላይ በ6 ዘዴዎች ለ400,000 በላይ ለክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በድግግሞሽ ስልጠና ተሰትቷል፡፡ 74 የጽሁፍና 164 የቃል የህግ ምክር የተሰጠና በድምሩ238 አቅም ለሌላቸውን ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ድጋፍ ተሰጥቷል፡፡ ከሰብአዊ መብት ማክበርና ማስከበር አንጻር ለ750 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል ከህገወት ሰውን ማዘዋወር መከላከል ውንጀል አፈጻጸም ጠፍልሰት ምክር ቤቱን መልሶ ማቋቋም ተችሏል፡፤የፍልሰት ምክር ቤት የትብብር ጥምረትን የቅብብልሎሽ ስርኣቱን ተዘርግቷል ይህም እስከ ወረዳ ድረስ ተሰርቷል፡፡ 150 ለሚሆኑ የፍትህ አካላት ስልጠና 6607 ለሚሆኑ ማህበረሰብ ክፍሎች በመድርክ እና በሚዲያ ተሰጥቷል፡፡ Read More